የጤና ዘርፍ ስራችንን ስንመለከት የእናቶችና ህፃናት ጤና ዋናው ተግባር ሲሆን ለ34,407 እናቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ለ33,895 ወይም 99% ማከናወን ተችሏል፤ የቅድመ ወሊድ ክትትል የጀመሩ እናቶች 8,943 ታቅዶ 8,288 አፈፃፀም 93%፤ በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጠውን የወሊድ አገልግሎት የሚያገኙ እናቶች 7,602 የታቀደ ሲሆን 2722 የእቅዱን 36% ማከናወን ተችሏል፡፡ የድህረ ወሊድ ክትትል አገልግሎት የሚያገኙ እናቶች የእቅዳችን 100% መፈጸም ችለናል፡፡ የነፍሰ ጡር እናየሚያጠቡ እናቶች የኤች አይ ቪ ምርመራ አገልግሎት የእቅዳችን 100% ፈጽመናል፡፡ ሁሉንም ዓይነት ክትባት አገልግሎት ያገኙ ህፃናት 8,490 ታቅዶ 7,579 የእቅዳችን 89% ተከናውኗል፡፡ የኩፍኝ ክትባት 2 ያገኙ ህጻናት 8,490 ታቅዶ 7,114 የእቅዱን 84% ተፈጽሟል፡፡ የእናቶችና ህፃናት ሞት ከሆስፒታሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በጤና ተቋም ላይ ዜሮ ማድረግ ተችሏል፡፡