Monday, August 17, 2026
መዲናችን አዲስ አበባ በሁለንተናዊ መልካም ገጽታ በዓለም መድረክ ላይ በግልጽ ያሳዩ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ እድገት ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግባለች ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ሐምሌ 3፣ 2018 ዓ.ም
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉና ቅልጥፍና እየታየባቸው መምጣቱን ተገልጋዮች ገለጹ።
የሰው ልጅ በተፈጥሮው መደመጥን ይሻል። ሰው ሲደመጥ የሚፈጠርበት ደስታ በሀገር ደረጃ ደግሞ ትርጉሙ የላቀ ነው። የሚደማመጡ ዜጎች ሀገራቸውን እፎይ ያሰኛሉ። በአንጻሩ የመደማመጥ ባሕል ከተሸረሸረ ጭቅጭቅ ይነግሳል።
የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት እና የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ ዘርፉ ለሌሎች ኢንዱስትሪዎችም የማይናወጥ መሠረት ሆኗል። ይኸው ወሳኝ እመርታ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አማካኝነት በሀገር በቀል መፍትሔዎች የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት መለወጥና የሀገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚቻል በተግባር እያሳየን ነው።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር አቅመ ደካማ ዜጎች የተሻለ የመኖሪያ አካባቢ እንዲያገኙ በሚደረገው የበጎ ፈቃድና የማህበረሰብ ተሳትፎ እንቅስቃሴ አካል፣ በቤት ቁጥር 631 ወ/ሮ ወርቅነሽ ሀይሉ እና በቤት በቤት ቁጥር 961 አቶ ድጋፌ አበባው የነበራቸው አሮጌና ለመኖሪያ አደገኛ የሆነ ቤት ፈርሶ በአዲስ የመገንባት ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት "በጎነት በተግባር" በሚል መሪ ቃል በወጣቶችና ስፖርት በኮሙኒኬሽ እና ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤቶች አስተባባሪነት የ2018 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ስራ በይፋ ተጀምሯል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ጥምር የፀጥታ አካላት ፣ ህዝባዊ የሰላም ስራዊት እና የሸገር ሲቲ ኢጀርሳ ጎሮ የፀጥታ አካላት በአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ::
አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት የትምህርት ዘርፉ ጥራትና ተደራሽነት ለማሳደግ ፣ የጤና ተቋማት ግንባታ ሂደት ፣ የወጣቶችና የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መስሪያ ቦታዎች በልዩ ትኩረት በማከናወን ላይ ነው።
የክፍለ ከተማው ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ለ2017/18 ዓ.ም ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅት በእንጦጦ ችግኝ ጣቢያ እያደረገ ይገኛል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት " ዓላማ ተኮር ኮሙኒኬሽን " ዙሪያ በ10ሩም ወረዳ ለሚገኙ ለዘርፉ አመራሮች ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የሲቪል ማህበራት ''ጠንካራ የሲቪል ማህበራት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ'' በሚል መሪ ቃል የማጠቃለያ መድረክ ውይይት ተካሄደ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለአጠቃላይ ለክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በአመራር ጥበብ እና በአመራር ውጤማነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ ።