በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀማሉ ጀምበር እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች በመስራት የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን በተጨማሪ እነዚህን መሠረተ ልማት ማድነቅ፣ ማበረታታት እና መንከባከብ አለብን በተመሳሳይ የኑሮ ውድነትን የሚቀርፋ ሰው ተኮር ስራዎች እና ስራ እድል ፈጠራ የህዝብ ተጠቃሚነት ላይ እንደ ከተማ የተለያዩ ስራዎች በስፋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።